Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት የተለያዩ ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር መሸጥ (ማከራየት) ይፈልጋል

Closing Date ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ቀንና ሰዓት
Opening Date ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ቀንና
Published On አዲስ ዘመን (Sep 24, 2023)
Region Sidama
Document Price 200
Bid Bond 10%

Tender Description

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከደንበኛ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን ማሸነሪዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር መሸጥ/ ማከራየት ይፈልጋል።

የጨረታው መመሪያ፡

1. ንብረቱን መግዛት/ መከራየት የሚፈልግ ተደራዳሪ የድርድሩን መነሻ ዋጋ 1/10ኛ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማቅረብ በድርድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

2. ከላይ የተጠቀሰውን ንብረት መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ተደራዳሪ የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማልከቻ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኃላ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከ400 ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ቀንና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ወርክ አውት ዲቪዥን ቢሮ በአካል በመቅረብ ማመልከትና መደራደር ይችላሉ።

3. ንብረቱን በከፊል ብድር መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ የባንክን የብድር መስፈርት ማሟላት ቢያንስ 20 በመቶና ከዚያ በላይ ቅድመ ክፍያ መክፈል ቀሪውን ክፍያ የሚያጠናቅቅበት ጊዜ እንዲሁም በዓመት ስንት ጊዜ እንዲሚከፍልና የአንድ ጊዜ ክፍያ ምን ያህል እንደሆነ መጠቀስ ይኖርበታል።

4. ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የድርድር ሽያጭ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ቀሪውን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የድርድር ጨረታ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

5. ተደራዳሪው በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል።በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

6. እጅ በእጅ/ በካሸ አሸናፊ የሆነው ተደራዳሪ በንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት።

7. የድርድሩ አሸናፊ በጥሬ ገንዘብ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠየቀውን ማንኛውንም ክፍያዎችና ቀረጥ መክፈል ይኖርበታል።

8. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251-46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

9. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የተገለጸዉን ጋዜጣ ይመልከቱ

የኢትጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት

Company Information

የኢትጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት

የኢትጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now