Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ በ2016 ዓ.ም. አላቂ ዕቃዎች ስቴሽነሪ ፣ የቢሮ ዕቃዎች ፈርኒቸር ፣ የተለያዩ የኤለክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሞተር ሳይክል ከህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Closing Date ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
Opening Date በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
Published On አዲስ ዘመን (Sep 22, 2023)
Region Sidama
Document Price 200
Bid Bond 20000

Tender Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ በ2016 ዓ.ም የተለያዩ ግዥዎችን በየሎቱ አከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1.ሎት 1. አላቂ ዕቃዎች/ ስቴሽነሪ፣

2.ሎት 2. የቢሮ ዕቃዎች ፈርኒቸር፣

3. ሎት 3. የተለያዩ የኤለክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣

4.ሎት 4. የሞተር ሳይክል ግዥዎችን ከህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤

2. ለአቅራቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3. የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤

4. የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬትና መለያ ቁጥር ያለው፤

5. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርቡ፤

6. ለእያንዳንዱ የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫዎች ስፔስፊከሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7.ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር /200/ ከፍለው መግዛት አለባቸው፡፡

8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 20,000 /ሃያ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሰፒኦ (CPO) ማስያዝ አለበት።

9.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና

10. ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማጠቃለል ማቅረብ አለባቸው።

11.የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 56 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ግዥ ፋ/ን/ አስ/ዳይሬክቶሬት በስልክ ቁጥር 046-221-2413 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

Company Information

ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ

ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now