Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚዘረጋው Automation የሚያገለግሉ Computer Networking ግብአቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Closing Date በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
Opening Date በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን (Sep 27, 2023)
Region
Document Price 100
Bid Bond 2%

Tender Description

 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 የይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚዘረጋው Automation 

የሚያገለግሉ ComputerNetworking ግብአቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

1.      ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤

2.     የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ የሚችሉ፤

3.     በጨረታ ለመወዳደር ከገቢዎችች እና ጉምሩክ የተሰጣቸውን ማስረጃ /የታደሰ ከሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4.     ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ

5.     ዶክመንቱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይ/ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ፋይ/ንብአስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

6.     የጨረታው ሰነድ በአንድ ትልቅ ፖስታ 1ኛ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት በአንድ ፖስታ 2ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶከመንት በአንድ ፖስታ 3ኛ ቴክኒካል ኮፒ ዶክመንት በሁለት ፖስታ 4ኛ ፋይናንሻል ኮፒ ዶክመንት በሁለት ፖስታ በሰም ታሽጎ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7.     የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ሕጋዊ የሆነ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በ15ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይ/ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.     ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 (ስድስት) ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል።

9.     የወቅቱ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ፤ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያዝ አለበት።

10.   አሠሪው መስሪያ ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0966 90 16 81 መደበኛ 046 225 0769 ይደውሉ።

Company Information

ይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል

ይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now