Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Closing Date ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ተኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት
Opening Date ጨረታው በ16ተኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡45
Published On አዲስ ዘመን (Sep 22, 2023)
Region Sidama
Document Price 100.00 ብር
Bid Bond Null

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ለፖሊስ መምሪያ እና ለኢንተርፕራዞች ኢን/ልማት መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ባቀዱት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት: -


1. የሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ፣ ሎት/ምድብ 01/2016

2. የሀዋሳ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ ፣ ሎት/ምድብ 02/2016

3. የሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንተርፕራዞች ኢን/ልማት መምሪያ ፣ ሎት/ምድብ 03/2016 ለቢሮ አገልግሎት እንድንከራይላቸው የጠየቁን ጽ/ቤትና መምሪያዎች ባቀረቡት መመዘኛ በሰነድ በተቀመጠው መሠረት የሚያሟሉትን ሕንፃዎችን የሚያቀርብ አቅራቢ መወዳደር ይችላል።

01. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

02. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ሲሆን፤

03. ተጫራቾች የ2015 ዓ.ም ድረስ የጣራ ግርግዳና የዓመቱ የቦታ ግብር የገበረበት ማስረጃ ማያያዝ አለበት።

04. የአከራይ ተከራይ ግብር መከፈሉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማያያዝ አለበት።

05. የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

06. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሽገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጨረታውን በግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

07. ጨረታው በ16ተኛው አሥራ ስድስተኛው/ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ በ3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

08. በተሸጠው ሰነድ ዋጋውን ሞልቶ ያስገቡ ፤ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።

09. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 1334

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ

ሀዋሳ

Company Information

Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መም

 Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ 

Phone +251 46 220 4235+251 46 220 0665+251 46 220 9740+251 46 221 5312
Mobile +251 91 198 4331
Fax +251 46 221 4902






Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now