Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ40 ሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት ግዥ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሆኖ በየሶስት ወር አፈጻጸም እየታየ የሚታደስ ውል በመግባት የአገልግሎት ግዥውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Closing Date በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
Opening Date በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:30
Published On አዲስ ዘመን (Sep 28, 2023)
Region Sidama
Document Price 200.00 ብር
Bid Bond 10,000.00 ብር

Tender Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ40 ሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት ግዥ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሆኖ በየሶስት ወር አፈጻጸም እየታየ የሚታደስ ውል በመግባት የአገልግሎት ግዥውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፣

1.      የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶእየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፣

5.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 (አስር ሺህ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ 800 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 የሚከፈት ይሆናል፣

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፣ ፊርማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው።

7.     መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ግዜ የግዥውን ብዛት (መጠን/ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር) መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው የምግብ ሜኑ ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።

 

9.     ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 221 6730 /046 220 1267 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የመ/ቤቱ
አድራሻ፡ ከኢሚግሬሽን ፊት ለፊት/ ከሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ግቢ ውስጥ ነው።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን

Company Information

National Regional Government Sports Commission የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን

National Regional Government Sports Commission
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን
Phone +251 46 221 6730


Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now