Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date ለ15 ተከታታይ የስራ ሰዓት እና ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
Opening Date በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 8፡00 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን (Oct 01, 2023)
Region Sidama
Document Price 50.00 ብር
Bid Bond 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፁትን በ2016 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች /ዳይሬክቶሬት/ሥራ ላይ የሚያስፈልገውን ከታች የተዘረዘሩትን

ማለትም፦

1.ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ውጤቶች /ቋሚ የቢሮ ቁሳቁስ/፣

2. የፅዳት እና ቢሮ ለውበት ሥራ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች

3.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ዲጅታላይዜሽን መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች ፣ Server Dell ፣ Desktop computer፣ Printer Cisco 2960–24/48/port፣

የጽህፈት መሳሪያ /ስቴሽነሪ/፣

4. ለተኝቶ ታካሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል ጤፍ ፣ ጥራጥሬ ፣ ዳቦ ፣ በርበሬ ፣ ዘይት ፣ ቅመማ ቅመም፣

5. ጨርቃ ጨርቅ ለሆስፒታሉ ደንብ ልብስ የሚውል፣

6. በየአስራ አምስት ቀን ወደ አዋሳ ጥቁር ውሃ ሲሊንደር ለማስሞላት የሚሄደውን የመኪና ኪራይ፣

7. ሕትመትና የህትመት ውጤቶች፣

8. የቧንቧ ዕቃዎች፣

9. የመድሃኒትና የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች፣

10. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች /Florccent Lamp, Electric Wire/; etc.

11. የሕክምና መሳሪያ እና አክሰሰሪ /መለዋወጫ/ ማሽኖችን ዕቃዎች በግልፅ የሀገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅደም ተከተል ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

የዘመኑን ማለትም የበጀት ዓመቱን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፣

2. ጨረታውን አሸንፎ የሚያቀርበውን ዕቃ/ንብረት ጥራቱን ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል፣

3. ጨረታውን ያሸነፈው ግለሰብ/አቅራቢ ድርጅት ዕቃውን/ ንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በራሱ ወጪ የሚያቀርብ መሆን አለበት።

4. አሸናፊ ሆኖ የሚጠራው ግለሰብ/ አቅራቢ ድርጅት የዕቃውን /ንብረቱን ጥራትና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠው መልኩ ውል ገብቶ በውሉ መሰረት የሚያቀርብ መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እንዲያስገቡና በተገለፀው ቀን የሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በመስሪያ ቤቱ ስም ለቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

9. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

10.ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚገባበት መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0926 38 48 50/ 0916 40 15 99/ 0916 37 27 54/ 0916 07 11 84/ ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል

Company Information

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Mobile

+251 93 052 7570
+251 90 685 9625

+251 91 637 2754

+251 92 706 3330

+251 92 638 4850

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now