Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ/ብ/ክ/መንግስት የስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት እና የጽህፈት መሣሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Closing Date ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
Opening Date በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን
Region
Document Price 100.00 ብር
Bid Bond በየሎቱ የተለያየ ነው

Tender Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/16

የሲዳማ/ብ/ክ/መንግስት የስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

-የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት እና

-የጽህፈት መሣሪያ ግዥ ለመፈጸም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትይፈልጋል።

በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣ የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች 

በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

-ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ 

ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡

-ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 

ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 100አንድ መቶ ብር/ ከፍለው በመግዛት 

ሰነዱን ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 804 መውሰድ ይችላሉ፡፡

-ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት

 ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና የፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል 

አንድ ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግና ሲፒኦ/ባንክ ጋራንቲ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ በመክተትና አጠቃላዩን በአንድ 

ትልቅ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 804 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመኪና ጥገና ጋራዥ ዋስትና C.P.O/ባንክ ጋራንቲ ብር 20,000/ ሃያ ሺህ/ እና የጽህፈት መሣሪያ ዋስትና C P.O/ባንክ ጋራንቲ ብር 10,000/አስር ሺህ ብር መሆን ይኖርበታል።

- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

 በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 804 ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ 16ኛው ቀን

 የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸግም ሆነ የመከፈቱ ሥነሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ

 ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል።

  -ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ 

    መብቱ የተጠበቀ ነው።

 አድራሻ፡- ሀዋሳ መስቀል አደባባይ ከፍ ብሎ መናኸሪያ ሌዊ ሆቴል ፊት ለፊት ሲዳማ ቡና ህንፃ ውስጥ ነው።

ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 046 212 2174

Company Information

በሲ/ብ/ክ/መ/ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

ሀዋሳ

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now