Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የመኖሪያ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Closing Date በ26/02/2016 ዓ.ም. ከ4፡00-6፡00 ሰዓት
Opening Date በ26/02/2016 ዓ.ም. ከ4፡00-6፡00 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን (Oct 04, 2023)
Region Sidama
Document Price Not defined
Bid Bond 25%

Tender Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ አለም ተክለብርሃን እና በአፈ ተከሳሾች እነ ወ/ሮ ለተብርሃን ገ/እግዚአብሄር 2 (ሰዎች) መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዳካ ቀበሌ ውስጥ በሟች ሀምሳ አለቃ ተክለብርሃን ስም ተመዝግቦ የሚታወቀው መኖሪያ ቤት ቦታ ስፋት 200 ካሬ ሜትር የሆነው በመነሻ ዋጋው 2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) እንዲሸጥ እና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ከ23/01/2016 ዓ/ም ጀምሮ አስከ 23/02/2016 ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ የሀራጅ ሽያጩ በ26/02/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

ስለሆነም፡-

      በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር

      የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

      1. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 115 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ።

      2. በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል።

      3. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።

      4. ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት

      ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሔድበታል፡፡

      5. ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የስም ዝውውር በፍ/ቤቱ ትእዛዝ ይፈፅምለታል፡፡

      6. ጨረታው የሚካሔደው በ26/02/2016 ዓ/ም 4፡00-6፡00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ከ/ከተማ ዳካ ቀበሌ ውስጥ በሟች ሀምሳ አለቃ ተክለብርሃን ስም ተመዝግቦ የሚታወቀው መኖሪያ ቤት እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

      በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር

      የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

      Company Information

      Sidama Regional State Supreme Court Hawassa High Court ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሀዋሣ ከተማ ከፍተ

      ......................................................................................

      Sponsored

      Featured Offers

      Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

      Comparing 0 / 3 products selected
      Compare Now