Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ብ/ክ/መ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2016 በጀት ዓመት ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የፅዳት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Closing Date በ16ኛው ቀን በ8፡30
Opening Date በ16ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን (Oct 08, 2023)
Region Sidama
Document Price 100.00 ብር
Bid Bond 2%

Tender Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 05/2015

የሲዳማ ብ/ክ/መ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2016 በጀት ዓመት በመደበኛ እና FSRP ፕሮጀክት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፤

2. ሎት 2 ፈርኒቸር፤

3. ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች፤

4. ሎት 4 የፅዳት እቃዎች፤

5. ሎት 5 ሌሎች አላቂ እቃዎች

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ።

1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና TIN ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልጸውን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሁለት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ተብሎ ተለይቶ ኦሪጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባችሁ።

5. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ለ30 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው።

6. ከላይ የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ ሆን አለባቸው።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ይታሸግና በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል። የኤሌክትሮኒክስ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ በዕለቱ የሚከፈት ይሆናል።

8. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀን ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ነው።

9. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሣብ መቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የመሠረተ መሆን አለበት። በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በሚለው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል።

10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሲ/ብ/ክ/መ/መስኖ ልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የሂሳብ ቁጥር 1000351753707 ገቢ በማድረግ በኤጀንሲው ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 09 ማግኘት ይቻላል።

11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ /የቀረበ/ ተጨማሪ ሰነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል። በመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፊርማና ማህተም ካልተደገባቸው የቀረበው የማወዳደሪያ ሃሣብ ይሰረዛል። በተጨማሪም ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን። አጠቃላይ የዕቃው ዝርዝርና ሲፒኦ ማስያዥያና ማብራሪያ በጨረታ ሰነድ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። በጨረታው ሰነድ ላይ ከተጠቀምነው እስፔክ ውጪ ተጨማሪ እስፔክ በእስክሪፕቶ መጻፍ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሆኖ ቢገኝ ግን ከውድድሩ ውጪ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ 1 - ወልደ አማኑኤል አደባባይ ፊት ለፊት አያልነሽ አለሶ ሞል 3ተኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-221-7860 መጠየቅ ይችላሉ።

የሲዳማ ብ/ክ/መ/መስኖ ልማት ኤጀንሲ

Company Information

Sidama National Regional State Irrigation Development Agency የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስኖ ልማት ኤጀንሲ

.

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now