Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ዘይትና ማለስለሻ ቅባት እና ባትሪዎች እንዲሁም የተሽከርካሪዎች ባትሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡15
Opening Date በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡45
Published On አዲስ ዘመን (Oct 09, 2023)
Region Sidama
Document Price 200.00 ብር
Bid Bond 50,000.00 ብር

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ግዥ ባቀዱት መሠረት የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ዘይትና ማለስለሻ ቅባት እና ባትሪዎች ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ለተሽከርካሪዎች የተለያዩ ዓይነት ዘይትና ማለስለሻ ቅባት፣ ሎት 01/2016

2. የተሽከርካሪዎች ባትሪ፡- ሎት 02/2016

በዚህ መሠረት፡-

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።

1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /የተመሰከረ/ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።

5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው ሲታሸግ ኤንቨሎፑ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 /ግዥ ኬዝ ቲም/ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡45 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውንሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 22 1334

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሀዋሳ

Company Information

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

Phone

+251 46 220 4235

+251 46 220 0665

+251 46 220 9740

+251 46 221 5312

Mobile +251 91 198 4331
Fax +251 46 221 4902

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now