Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀ/ቅ/ጽ/ቤት 2016 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት ለመጠቀም ባለ ሦስት ኮከብ እና ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች አወዳድሮ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Closing Date ለ15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን
Opening Date በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን
Region Sidama
Document Price 100
Bid Bond 20000

Tender Description

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀ/ቅ/ጽ/ቤት 2016 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት ለመጠቀም ባለ ሦስት ኮከብ እና ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች አወዳድሮ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈለ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎች አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

*ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) አንደኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 210 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

*ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) (በሲ.ፒ.ኦ) ያስያዙበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

*በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣ ለ15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

*ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አንደኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

*የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል።

*ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ስልክ ቁጥር 046-220-4224 ይጠቀሙ። አድራሻ- አሮጌ ገበያ አለ በጅምላ 100 ሜትር ወረድ ብሎ

Company Information

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀ/ቅ/ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀ/ቅ/ጽ/ቤት

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now