Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

ፎረም ኦን ሰስተነብል ቻይልድ ኢምፓወርመንት በድሬዳዋና ወላይታ ለሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች አገልግሎት ላይ የሚውል ኮምፒውተሮችንና የቢሮ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት
Opening Date Oct 27, 2023 2:30 PM
Published On Reporter
Region Addis Ababa
Document Price 300
Bid Bond 2%

Tender Description

የሰነድ ቁጥር 0008

የግዥ ጨረታ ሰነድ

ፎረም ኦን ሰስተነብል ቻይልድ ኢምፓወርመንት በድሬዳዋና ወላይታ ለሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች አገልግሎት ላይ የሚውል ኮምፒውተሮችንና የቢሮ ቁሳቁሶችን በጫረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የሚፈለጉ ዕቃዎች ዓይነት ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።

1ኛ. ላፕቶፕ ኮምፒውተር (Hp Core i5)፡

2ኛ. ዴስክ ቶፕ ኮመፒውተር(Dell OptiPlex Core i5)፡፡

3ኛ. ፕሪንተር (Laser Jet 400)፡፡

4ኛ. የቢሮ ወንበሮች (Laser Jet 400)፡፡

5ኛ. የቢሮ ጠረጴዛ (Laser Jet 400)፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በተፈለገው ዓይነትና መጠን ለማቅረብ ፈየሚፈልግ ተጫራች ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ እና የተመረተበት ሀገር በዋጋ ማቅረቢያ ላይ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

1. ተወዳዳሪው ምርቱን እንዲያመርት ወይም እንዲያቀርብ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለውና ሰርተፊኬቱ ላይ በግልፅ የተቀመጠ በባለሥልጣኑ እውቅና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

2. የአቅራቢው ስም፣ አርማ፣ አድራሻ (ስልክ ቁጥርን ጨምሮ እና የምርቱ ስም መገለፅ አለበት፡፡

3. ምርቱ ከምን እንደተመረተ መገለፅ ይኖርበታል። እንዲሁም የምርቱ ማሸጊየ ንፁህ መሆን አለበት

4. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሥራ ላይ ተሰማርተው መልካም አፈፃፀም ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በድርጅቱ ሥም የባንክ ሲ ፒ ኦ ማያያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጫረታ ሰነዳቸውን በታሸገና በተፈረመ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

ተጫራቶች ሊያሟሉ የሚገባቸው ተጨማሪ መስፈቶች

1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት

2. የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር/የቲን ቁጥር/

3. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቶችች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚሰጡትን ዋጋ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ አጠገብ በሚገኘው ብርሃን ባንክ ያለበት ህንፃ 5ኛ ፎቅ ዋናው ቢሮ አስተዳዳርና ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫና ዋጋ ማቅረቢያ በማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር) እየገዙ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. አሸናፊ ተጫራቾች በዝርዝር ያቀረቡትን ዕቃዎች ውል ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

Company Information

ፎረም ኦን ሰስተነብል ቻይልድ ኢምፓወርመንት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 833 3926 / 011 833 3927/28 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now