Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኤሌክትሮኒክስ ፣ አንቲ ቫይረስ ፣ ሞተር ሳይክል እና ፈርኒቸር መግዛት ይፈልጋል

Closing Date 29/10/2023
Opening Date 30/10/20023
Published On AddisZemen
Region Sidama
Document Price 100
Bid Bond 10,000

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2016

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ እቃዎችን:

ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ

ሎት2. አንቲ ቫይረስ

ሎት 3 ሞተር ሳይክል

ሎት 4 ፈርኒቸር

በዚሁ መሰረት፡-

1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ

2.የቫት VAT ፣ ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለው

3. የግብር ከፋይ/TIN/ መለያ ቁጥር ያለው

4. የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀስውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር)ብቻ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 37 በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይቻላል።

7.ተጫራቾች መወዳደር ለሚፈልጉት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO/ BD BOND የ90 ቀን/ ለያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ የሚችል

8.ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጂናል 1 ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9.ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡

10.የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዝን ማስገባት ይኖርበታል፡፡

11.የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል።

12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 5584 መጠቀም ይቻላል፡፡

Company Information

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት Company Info

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት



Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now