Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ ሞተር ሳይክል ፣ የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ዕቃዎችን ለመግዛትና ተሽከርካሪዎችን በእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Closing Date በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30
Opening Date በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 8:30
Published On አዲስ ዘመን
Region Sidama
Document Price 100
Bid Bond እንደየሎቱ

Tender Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2016

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሎት፡

ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ

ሎት 2 ፈርኒቸር

ሎት 3 ሞተር ሳይክል

ሎት 4 የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ዕቃዎችን ለመግዛትና ተሸከርካርዎችን በእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት መሣተፍ ይችላሉ፡፡

1. ከላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በየዘርፍ ሥራዎች የተሰማሩ ፣ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በገቢዎች ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታhስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤

3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና ሎት 4 ለእያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ብር /5,000.00/ ለሎት 2 እና ሎት 3 ለእያንዳንዳቸው ብር 2,500/ሁለት ሺህ አምስት መቶ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

4. አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈር የውል ማስከበርያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡

5. ለተሽከርካሪ ጥገና ሀዋሳ ካሉት ጋራዦች ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እና የሲዳማ ብ/ክ/መ/ የትራንስፖርት ቢሮ የሰጣቸውን ብቃት ማረጋገጫ ደረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው። 6. ተጨራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 07 ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ የጨረታ ሠነዱን የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኦሪጂናልና ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የሎት 4 (አራት) ወይም የመኪናና ጥገና የእጅ ዋጋ ቴክኒካሉና ፋይናንሻሉን በተለያዩ ኤንቨሎፕ ከታሸገ በኃላ በአንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማሸግ አለባቸው በዕለቱ የሎት 4 ቴክኒካሉን ክፍል ብቻ ይከፈታል፡፡

9. የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16 /አስራ ስድሰተኛው/ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡

10. ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ ዋጋ የሚፀናበትን ከ45 ቀናት በታች የጊዜ ገደብ መስጠት የለበትም፡፡

11. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል፡፡

12. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ7 /ሰባት/ ቀን በኃላ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል፡፡

13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እያንዳንዳቸውን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 10 ቀናት ድረስ በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በተፈለገው በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኃላ ማስረከብ አለበት፡፡

14. አቅራቢው የውል ግዴታውን መሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ ክፍያው ወዲያውኑ በቼክ ይከፈለዋል፡፡

15. አቅራቢው የውል ግዴታውን መሉ በሙሉ አለመፈፀሙ ሲረጋገጥ በውል ግዴታው መሰረት በህግ አግባብ ይቀጣል፡፡

16. ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የስልክ ቁጥር 046-220-0072

Company Information

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ


Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now