Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ፈርኒቸር ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡15 ሰዓት
Opening Date በ16ኛው ቀን በ3፡45 ሰዓት
Published On አዲስ ዘመን
Region Sidama
Document Price 200
Bid Bond 50000

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ከንቲባ ጽ/ቤት በ2016 በጀት አመት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ፈርኒቸር ዕቃዎች ባቀዱት መሠረት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች፡-

ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ - ሎት 01/2016

ፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ፡- ሎት 02/2016

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣

3.የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

4.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡

5.የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

6.ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው በ16ተኛው ቀን በ3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ3፡45 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

8.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 046 212 1334

Company Information

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now