Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የአዶላ ወዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የቋሚ እቃዎች(Furniture) እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Closing Date differ for each lot
Opening Date differ for each lot
Published On AddisZemen
Region
Document Price 200
Bid Bond differ for each lot

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

-አላቂ እቃዎች ፣

የጽዳት እቃዎች ፣

-ኤሌክትሮኒክስ ፣ የቋሚ እቃዎች(furniture) እና 

-የደንብ ልብስ ለ2016 በጀት አመት በግልጽ ጨረ‎ታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ቀርባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ::

1.ተጫራቾች በዚህ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ስለመሆናቸው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2.ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ ::

3.ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት በመደበኛ የስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከአዶላ ወዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የግዥ ዋጋ 1% በአዶላ ወዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከዋናው (Original) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታው አሽናፊ ከተለየ በኃላ ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ጨረታውን ላሸንፋት የሚመለሰው ደግሞ የውል ማስከበሪያ በአዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት ካስገቡ በኃላ ነው::

5.የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፓስታ (envelope) ዋናውን ና ኮፒውን ለያይቶ ይህን ማስታውቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ጨረታው 5 የስራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 በአዶላ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ና ተዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስረአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም፡፡

6.የኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎች ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፓስታ (envelope) ዋናውንና ኮፒውን ለያይቶ ይህን ማስታውቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው 15 የስራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው ወይም ከአንድ ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 በአዶላ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገንዘብ ጽ/ ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ- ስረአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡

7.የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን እቃ በታዘዘው ጥራት እና ብዛት መሰረት አዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ያስረክባል፡፡

8.ጨረታው የሚካሄደው በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ይሆናል፡፡

9.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

10.ስለ ቀድሞ መልካም አፈጻጸም መረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ያቀረበ ተወዳዳሪ ዋጋና ቴክኒካል ከሌላው ተወዳዳሪ ጋር እኩል ቢሆን ቅድሚያ ላቀረበው ይሰጣል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 335 0773

የአዶላ ወዩ ገንዘብ ጽ/ቤት

Company Information

የአዶላ ወዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now