Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
Opening Date በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
Published On addis zemen
Region Sidama
Document Price 50
Bid Bond 10000

Tender Description

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ

የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት፤

-በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

-የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው

-የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው

-የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

-ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴከኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና

2 ፎቶ ኮፒ በA4 ወረቀት ለአንድ ወረቀት አንድ ኮፒ ብቻ በማድረግና በማዘጋጀት እያንዳንዱን በተናጠል በፖስታ በማሸግ በፖስታው ውጭ የሰነዱን ዓይነት አሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመፃፍ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

--ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ CPO ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀ የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫዎች የያዘ ሰነድ /Specification / ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር ብቻ) ከፍለው በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታቸሁን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ በድርጅቱ የዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ ፖስታውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ16ኛው ቀን እስከ 6:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እንዲያስገቡ እያሳሰብን ጨረታው 6:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፦ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሎም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ስልክ፦ 046 212 1127

Company Information

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now