Welcome to Merkatomarket

Help & Settings
Customer Service Contact Us
Back to Tenders

የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የስልጠና ዕቃዎችና መሣሪያዎች እንዲሁም አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Closing Date 2025-07-12
Opening Date 2025-07-04
Published On 2025-07-01
Region Sidama
Document Price 300
Bid Bond 40000

Tender Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ በሔራዊ ከልላዊ መንግስት የሥራ ከህሎት ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2016 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ

-የስልጠና ዕቃዎችና መሣሪያዎች እንዲሁም

-አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊየሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና (TIN) ያላችሁ ፤ (የተጨማሪ እሴት ታክስ/ VAT) ተመዝጋቢ የሆናችሁ ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈለበት ከሊራንስ ከሚለከተው አካል ማስረጃ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከኮሌጁ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር ብቻ በመከፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በመጫረቻ ሰነድ ላይ ዋጋ በግልጽ በመፃፍ በጥንቃቄ ድልዝ ሰረዝ ሳይኖርበት በመሙላትበእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታውን በማሸግ አሪጅናሉንና ኮፒውን ለይቶ በመፃፍ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስበከሪያ ዋስትና እውቅና ካለው ባንክ CPO ገንዘብ 40,000 /አርባ ሺህ/ ብር ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

አሸናፊ ተጫራች ከኮሌጁ ጋር ውል ለመፈረም አሸናፊነቱን በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ካሸነፈው ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የገንዘብ ዋስትና CPO በባንከ የተረጋገጠ አሰርተው ለኮሌጁ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) የሥራ ቀናት ከፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡ 30 እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ከፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ6:40 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በኮሌጁ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ-32 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

አስራ ስድስተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከላይ የተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ላይ የሚከፈት ይሆናል።

ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች እስከ ኮሌጁ ግቢ ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ በባለሙያ አስፈትሾ የማስከረብ ግዴታ አለበት።ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠበ መረጃ:-አድራሻ:- በሲዳማ ብ/ክ/መ/በዳዬ ከተማ አስተዳደር የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Company Information

ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Sponsored

Featured Offers

Handpicked adverts designed to help you discover the best opportunities fast.

Comparing 0 / 3 products selected
Compare Now